Tuesday, May 1, 2012

አንድ ህዝብ አንድ ሀገር

ይህ የጡመራ ድረ-ገፅ (Blog) በዋናነት የተለያየ እምነት፣ ባህልና  ቋንቋ  ያላቸዉ አምስት ግለሰቦች በጋራ የሚጦምሩበት መድረክ ነዉ። በመሆኑም በዘርፈ-ብዙ ሀገራዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ግለሰባዊ ምልከታዎች የሚቀርቡበት ሲሆን ሌሎች በርካታ ኪነጥበባዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ እና ስነ-ጽሁፋዊ ስራዎችና እሳቤዎችም ይስተናገዱበታል። በአንድ ሀገር ዉስጥ የሚኖር ሕዝብ ምንም እንኳን የተለያዬ እምነት፣ባህልና ቋንቋ ተከተይና ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች ጥርቅም መሆኑ እሙን ቢሆንም ከነዚህና  ከሌሎች ተጨማሪ  ልዩነቶች ባሻገር ሌሎች በርካታ ለድርድር የማይቀርቡ የጋራ ሀገራዊ ጉዳዮችም ሊኖሯቸዉ እንደሚገባ /እንዳሉዋቸዉ/ ሌላዉ የማይካድ ሀቅ ነዉ። ነገር ግን ይህንን በልዩነት ዉስጥ ያለን ሀገራዊ አንድነት ለአደጋ የሚያጋልጡ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም ከሁሉም በላይ ግን በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለዉ ጉዳይ ዜጎች ካሉዋቸዉ የጋራ አንድነቶች ይልቅ ባሏቸዉ ጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ብቻ የማተኮር አዝማሚያና በዚህም ምክንያት የዘረኝነትና የጎሰኝነት መንፈስ በማስፋፋት ለአምባገነን ገዢዎች ስልጣን ማራዘሚያና መጠቀሚያ የመሆብ ሰለባ ነዉ።  ማንም ይህንኑ እዉነታ መሰረት አድር ሀገራችንን ኢትዮጵያን ያለቸበትን ሁኔአታ ቢመረምር በግምባር ቀደምትነት ሊጋፈጣቸዉ ሚችላቸዉ በርካታ እዉነታዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወድህ  እየተስተዋለ የመጣዉን የዘረኝነትና የመከፋፈል አደጋዎች ይሆናል። ይህንንም ጉዳይ   ልብ ብሎ ላስተዋለ ማንኛዉም ሰዉ ወዴት እያመራን እንደሆነ ለመገመት ነብይነትን የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም።

ሌላዉ ቀርቶ ትናንት ያሰብንበት ያደርሱናል ያልናቸዉና ዋጋ የከፈልንላቸዉ መሪዎቻችን እንኳን አምነን የሰጠናቸዉን ሀገራዊ አጀንዳዎች በትነዉ በራሳቸዉ ግለሰባዊ ጉዳዮች ሲነታረኩና አንዱ አንዱን ሲያጥላላ ከማየት፣ ከመስማትና ከማንበብ በላይ አሁን ያለንበት ሁኔታ ሊያስረዳና ሊጠቀስ የሚችል  ሌላ ምሳሌ አይኖርም። ችግሩን በጣም የከፋና አሳዣኝ የሚያደርገዉ ደግሞ ልዩነቶች ከተፈጠሩ በሗላም እንኳን ተቀራርቦ ለመዎያየትና ልዩነቶችን አጥብቦ በጋራ ለመስራት አንዳችም ፍላጎት አለማሳየተቻዉ ሲሆን ይህም ያለንበት ሁኔታ ምን ያህል አሳሳቢና አሌ ሊባል የማይገባዉ ጉዳይ መሆኑን ይበልጥ አመላካች ነዉ። በመሆኑም የዚህ ጦማር ዋና አላማ  ምንም እንኳን በአንድ ሀገር ዉስጥ የሚኖሩ ሰዎች የተለያየ እምነት፣ ባህልና ቋንቋ  ተከታይና ባለቤት ቢሆኑም፣ ልዪነታቸዉን እያከበሩ የጋራ በሆኑ ሌሎች በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብዙ ሆነዉ እንደ አንድ መስራት እንደሚችሉ ማሳዬትና የተጋረጠብን የዘረኝነትና የመከፋፈል አደጋ ፊለት ለፊት መጋፈጥና ግንዛቤ ማስጨበጥ ነዉ።

ጦማሩ  “አንድ-ሕዝብ አንድ-ሀገር” የሚል አርዕስት እንዲኖረዉ የተደረገዉም  ከዚሁ መንፈስ በመነጨ ሀሳብ ሲሆን ጦማሩን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በቋሚነት ከሚከትቡት አምስት መስራች ግለሰቦች በተጨማሪ ማንም ፈቃደኛ የሆነ ሰዉ ሊያስተላልፈዉ ወይም ሌሎች ቢያነቡትና ቢገነዘቡት ይጠቀማል የሚለዉ ሀሳብ በዚህ ጦማር በኩል ለ አንባቢያን እንዲደርስለት ከፈለገ በኢሜል አድራሻችን በኩል ጽሁፉን ቢያደርሰን፣ ጽሁፉ ለዚህ ጦማር የሚመጥንና አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ  የባለቤትነቱን መብት ሙሉ ለሙሉ ጽሁፉን ላደረሰን ሰዉ በመስጠት በዚህ ብሎግ እንዲዎጣ ይደረጋል።
አንድ-ህዝብ-አንድ-ሀገር!
ግንቦት 2012.

------------------------------------------------------------------------------- -------------------------------------------------------------------------------

No comments:

Post a Comment