መጸሐፍ ቅዱስ በአለማችን በብዛት ከተነበቡና
ወደ በርካታ የተለያዩ የአለም ቋንቋዎች ከተተረጎሙ መጸሐፍት መካካከል አንዱና ምናልባትም በአንደኝነት ሊጠቀስ የሚችል መጸሐፍ መሆኑ
አያጠራጥርም። ምንም እንኳን መጸሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈዉ? የሚለዉ ጥያቄ በተለያዩ ሰዎች የተለያየ መልስ የሚሰጥበት አከራካሪ ጉዳይ
ቢሆንም እንደዛሬዉ መጸሐፍት እንደልብ ባልነበሩበት ዘመን ለብዙዎች
የጥበብ ምንጭና የእምነት መንገድ ጠራጊ የሆነ፣ ዛሬም ድረስ ክርስትናን የእምነት ፍልስፍናቸዉ መሰረት ላደረጉ በርካታ የእምነቱ
ተከታዮች የእምነት-ማዕዘን በመሆነ እያገለገለ ያለ ታላቅ መጸሐፍ ነዉ፣ መጸሐፍ ቅዱስ። መጸሐፍ ቅዱስ በዋናነት ብሉይ-ኪዳንና አድስ-ኪዳን በሚባሉ ሁለት መሰረታዊ ክፍሎች (ቅጾች) የተዋቀረ
መጸሐፍ ሲሆን እነዚህም ሁለት ቅጾች እያንዳንዳቸዉ በርካታ ምራፎችንና የመጸሐፍ ክፍሎችን በዉስጣቸዉ አካተዉ የያዙ ናቸዉ። ከነዚህ በርካታ የመጸሐፍ ክፍሎች መካከል “መዝሙረ ዳዊት” በመጀመሪያዉ የመጸሐፍ ቅዱስ ቅጽ (በብሉይ ኪዳን) ስር ተካቶ የሚገኝ የመጸሐፍ
ቅዱስ ክፍል ሲሆን ምንም እንኳን “መዝሙረ ዳዊት” መቸና በማን ተጻፈ የሚለዉ ጉዳይ አከራካሪና እራሱን የቻለ ጥናትን የሚፈልግ ጉዳይ ቢሆንም
በዋነኝነት ግን ንጉስ ዳዊት አምላኩን እግዚያብሔርን ከፍ ከፍ ያደረገባቸዉና ያመሰገነባቸዉ ዉብ የዉዳሴና የምስጋና ዝማሬዎች (150) የተጠናቀሩበት መጸፍ ነዉ የሚሉ ሰዎች በአንድ ወገን ሲኖሩ በሌላ ወገን ደግሞ “መዝሙረ ዳዊት” ከዉብ የምስጋናና የዉዳሴ ቃላቶቹም በላይ ብዙዎች የማያዉቋቸዉን ጥበባት ያመቀና የብዙ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ የሆኑ ምስጥሮችን በእያንዳንዱ የዝማሬ ቃል ዉስጥ አምቆ የያዘ የመጸሐፍ ቅዱስ ክፍል ነዉ ብለዉ የሚከራከሩም አሉ።
በዋነኝነት ግን ንጉስ ዳዊት አምላኩን እግዚያብሔርን ከፍ ከፍ ያደረገባቸዉና ያመሰገነባቸዉ ዉብ የዉዳሴና የምስጋና ዝማሬዎች (150) የተጠናቀሩበት መጸፍ ነዉ የሚሉ ሰዎች በአንድ ወገን ሲኖሩ በሌላ ወገን ደግሞ “መዝሙረ ዳዊት” ከዉብ የምስጋናና የዉዳሴ ቃላቶቹም በላይ ብዙዎች የማያዉቋቸዉን ጥበባት ያመቀና የብዙ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ የሆኑ ምስጥሮችን በእያንዳንዱ የዝማሬ ቃል ዉስጥ አምቆ የያዘ የመጸሐፍ ቅዱስ ክፍል ነዉ ብለዉ የሚከራከሩም አሉ።
በሁለተኛዉ ረድፍ ከሚሰለፉ ተከራካሪዎች መካከል ብዙዎቹ ማንም ሰዉ ትክክለኛዉን አካሄድ ተከትሎ መተግበር
ከቻለ በእያንዳንዱ መዝሙር ዉስጥ ተመስጥሮ የሚገኘዉን ምስጥር ማግኘትና በህይዎቱ ብዙ ስኬቶችን መቀዳጀት እንደሚችል በዋናነት ይጠቅሳሉ።
ከነዚህም ምስጥራት መካከል ከእስር መፈታት፣ እናቶች በርግዝና ወቅት
ዉርጃ አሊያም ሌላ ችግር ሳይገጥማቸዉ በሰላም እንዲወልዱ ማስቻል፣ በንግድ ዉጤታማ (ስኬታማ)መሆን፣ ወደ ሌላ ሀገር የሚደረግን
ጉዞ ሰላማዊና የተሳካ እንዲሆን ማድረግ፣ በፍርድ ቤት ክርክር (ሙግት) መርታት መቻል፣ ግርማ መጎስን መላበስና በተቃራኒ ጾታ ተፈቃሪ
መሆን፣ጠላቶችን ማስወገድ (ድል) ማድረግ፣ርኩስ መንፈስን ማስዎጣትና የተለያዩ ህመሞችን መፈወስ መቻል የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በሀገራችንም ተመሳሳይ እሳቤ መኖሩ እሙን ቢሆንም
እራሱን የቻለ ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠንና
በቂ የህትመት ስራዎች ባለመኖራቸዉ ደፍሮ ብዙ ማለት አይቻልም ከዚህ ይልቅ ምናልባትም ይህን አይነት እሳቤ ከሚያጠናክሩ የዉጭ የህትመት
ስራዎች መካከል ከዛሬ ሰላሳ አመት በፊት (እ.ኤ.አ በ1982 ዓ.ም) ታትሞ ለንባብ የበቃዉ የጎድፍሬይ ሰሊንግ (Godfrey Selig) “የመዝሙረ ዳዊት ሚስጥሮች” (Secrets of the Pslams) መጸሐፍ አንዱ ሲሆን በዚሁ መጸሐፍ ዙሪያ
አንዳንድ ነጥቦችን እያነሳን ጥቂት ነገሮችን እንጨዋወት።
“በአንድ ወቅት ጥበበኞች፣ በእዉቀት
የነቁና የበቁ ካባሊስቶች ይኖሩ እንደነበር እንዳንዶችም አሁንም ድረስ እንዳሉ ማንም ሊክደዉ የማይችል ሀቅ ነዉ።” (It cannot be
denied that true, wise and enlightened Kabalists lived at one time, and that
some still live). ሲል ይጀምራል ጎድፍሬይ ስሊንግ በ“የመዝሙረ ዳዊት ምስጥሮች” መጸሐፉ መግቢያ ላይ። ሆኖም ግን
ይላል ጎድፍሬይ ሲቀጥል “ሆኖም ግን እነዚህ ጥበበኛ ካባሊስቶች ይህን
ታላቅ እዉቀት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ በመሸጥ ሀብትን ከማከማቸት ይልቅ ዘዎትር የመንፈሳዊ አለምን የጥበብ አዝመራ ከሚገበዩበት ከሰለሞን ቤተመንግስት ሳይርቁ ባዶ እጃቸዉን መቀመጥ ይበልጥ
ያስደስታቸዋል፣ ይህም እነሱ እራሳቸዉ እንደሚሉት በስተመጨረሻ ከሁሉም የሚልቀዉን፣ ማንም ያላየዉንና ከላይ የሆነዉን የጥበበብን
ሸማ ለመጎናጸፍ ያስቸላዋልና ነዉ።” ይላል።
በመሆኑም የጎድፍሬይ “የመዝሙረ ዳዊት ምስጥሮች” መጸሐፍ ዋና የማጠንመኛ ሀሳብ የጥንታዊ አይሁድ
ካባሊስቶች መንፈሳዊ ጥበብና ፍልስፋና ሲሆን ይህም የጥንታዊ ካባሊስቶች የእምነት ፍልስፍና፣ ስሞች የራሳቸዉ የሆነ የተደበቀ ሀይል
(ምስጥር) አላቸዉ የሚል ዋነኛ እሳቤ አለዉ። በመሆኑም እንደ እነዚህ ጥንታዊ አይሁዳዊያን ካባሊስቶች እምነት እግዚያብሔር፣ መላእክቶችና
ሌሎች መናፍስቶች (ለምሳሌ ሰይጣን) በግልጽ ከሚታወቁት የመጠሪያ ስሞቻቸዉ በተጨማሪ ሌሎች ልዩ (ድብቅ) ስሞች ያሏቸዉ ሲሆን እነዚህኑ
የተደበቁ ስሞች በትክክለኛዉ ቋንቋና ቅላጼ (pronouncetion) መጥራት የሚችል ማንኛዉም ሰዉ የፈለገዉን ነገር ማስፈጸም ይችላል
የሚል መሰረታዊ አንድምታ አለዉ።
እንደ ካባላዊያኑ አምነት ከሆነ ደግሞ እግዚያብሔር ለሙሴ በሲና ተራራ በድንጋይ ላይ ጽፎ ከሰጠዉ
አስርቱ ትዛዛቶች በተጨማሪ በቃል ብቻ የነገረዉ ሌሎች በርካታ ህግጋቶችና ሚስጥሮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሰዉ ልጅን መልካም
ሃሳብ ማስፈጸም የሚችሉ ድብቅ የእግዚያብሔርና የመላእክት መጠሪያ ቅዱስ ስሞች ይገኙበታል። በመሆኑም ይህ ሚስጥር ከሙሴ ጊዜ ጀምሮ
በቃል ከልጅ ልጅ ሲተላለፉ የቆየና እዚህ የደረሰ ጥበብ በመሆኑ ጥንታዊ (kabala) በሚል ስያሜ መጠራት ጀመረ በማለት ያብራራሉ።
የጎድፍሬይ “የመዝሙረ ዳዊት ሚስጥሮች” መጸሐፉ በመግቢያዉ ላይ በነዚህና በሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ አንባቢን ግንዛቤ ካስጨበጠ
በሗሏ …በዚህ መጸሐፍ ዉስጥ የተቀመጠዉ ሁሉ እንደ ጸሐይ የሚያበራ
ታላቅ እዉነት አንጅ ተጨማሪ ማብራሪያና ገለጻ የሚጠይቅ የፈጠራ ወሬ ባለመሆኑ ማንም በሀላፊነት ሊጠቀምበት ይገባል የሚል
ማሳሰቢያን በማከል መጸሐፉን ለመጠቀም ከመሞከር በፊት ሊደረጉ የሚገቡ ያላቸዉን እንዳንድ ጥንቃቄዎችን በመዘርዘር ወደ ዋናዉ ጉዳይ
ይንደረደራል። ምንም እንኳን በመጸሐፉ ዉስጥ ከ 150 በላይ የሚሆኑ
መዝሙሮች ስላላቸዉ ጠቀሜታና ሚስጥር ትንተና የቀረበ ቢሆንም ለግንዛቤና ለምሳሌ ያክል ሶሰት የሚሆኑ ምሳሌዎችን ብቻ በመዉሰድ እንመልከትና
ምልከታችንን እናብቃ።
PSALM
TO PROTECT FROM HARM WHEN A VICIOUS DOG ATTACKS YOU
PSALM 58. - If
you should be attacked by a vicious dog, pray this Psalm quickly, and the dog will
not harm you.
(ተናካሽ ዉሻ በገጠመ ጊዜ እራስን
ለመከላከል የሚጸለይ መዝሙር
መዝሙር 58፡
አደገኛና ተናካሽ ዉሻ ከገጠመህ በዚህ ምዕራፍ የሰፈረዉን መዝሙር በፍጥነት ጸልይ ዉሻዉም ምንም አይነት ጉዳት አያደርስብህም።)
PSALM
TO BE SUCCESSFUL IN BUSINESS
PSALM 8. - If
you wish to secure the love and good will of all men in your business transactions,
you should pray this Psalm three days in succession after sundown, and think
continually of the Holy name of Rechmial, which Signifies great and strong God
of love, of grace and mercy. Pronounce at each time the appropriate prayer over
a small quantity of olive oil, and anoint the face as well as the hands and
feet. The letters, composing the holy name are found in the words: Addir, verse
2; Ja reach, verse 4; Adam, verse 5; Melohim, verse
6; Tanischilenu, verse 7. The prayer reads as follows: May it please thee, Oh,
Rechmial Eel, to grant that I may obtain love,
grace and favour in the eyes of men according to thy
holy will. Amen ! - Selah ! -
(በንግድ ስኬታማ ለመሆን የሚጸለይ
መዝሙር
መዝሙር 8፡ በንግድ አለም ዉስጥ በሚኖርህ
እንቅስቃሴ ስኬታማ ለመሆንና የሁሉንም ሰዉ መልካም ፈቃድና ትብብር ለማግኘት የምትሻ ከሆነ በዚህ ምዕራፍ ስር የሰፈረዉን መዝሙር
ሳታቋርጥ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ማታ ማታ መጸለይ ይኖርብሃል። በጾለትህም ወቅት ሳታቋርጥ ታላቅና ጠንካራ የፍቅር፣ የክብርና የምህረት
አምላክ ምልክት የሆነዉን ረቺሚያል (Rechmial) የሚለዉን ቅዱስ ስም በልብህ አስታዉስ። በተጨማሪም ከዚህ
ጽሁፍ መጨረሻ ላይ የቀረበዉን ጾለት በትንሽ የወይራ ዘይት ላይ አብረህ እየደገምክ ፊትህን፣ እግርንና እጅህን ተቀባ። ለዚህ ፆለት
የሚሆነዉን ቅዱስ ስም የመሰረቱት ፊደላት የተገኙት አዲር (Addir) ቁጥር 2፣ ጃ ሪች (Ja
reach)
ቁጥር 4፣ አዳም (Adam) ቁጥር 5፣ ሜሎሂም (Melohim) ቁጥር 6 እና ታኒስቺለኑ (Tanischilenu) ቀጥር 7 ላይ ሰፍረዉ ከሚገኙት
ቃላቶች ላይ ፊደላትን በመዉሰድ ነዉ። ከዚህ መዝሙር ጋር አብሮ የሚጸለየዉ
ጾለት እንድህ የሚል ነዉ … ስምህ የተባረከ ይሁን ኦ ረቺሚያል ኤል፣ እነሆ በሰዉ ልጆች ፊት ፍቅርን፣ ሞገስንና ክብርን አገኝ
ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁን። አሜን!- ሰላህ!.)
PSALM
WHEN POSSESSED BY AN EVIL SPIRIT
PSALM 66. - If a
man is possessed of a Ruack Roah (evil spirit), write this Psalm on parchment
and hang it upon him; then stretch your hands over him and say: Save me, 0 God,
for the waters are come into my soul.
(በክፉ መንፈስ ለተያዘ ሰዉ የሚጸለይ መዝሙር
መዝሙር 66፡
ክፉ መንፈስ ላደረበት (ለያዘዉ) ሰዉ በዚህ ምእራፍ ስር የሰፈረዉን መዝሙር በቆዳ ላይ ጻፍና ህመምተኛዉ ላይ እሰረዉ ከዚያም እጅህን
በህመምተኛዉ ላይ ጫንና እንድህ በል፣ አድነኝ ኦ አምላኬ ዉሃዎች ወደ ነፍሴ መተዋልና።)
በጣም እናመሰግናለን እንደዚህ አይነት ጥበቦች እኛ አገርም ሞልተው ተትረፍርፎዋል ጥናት አልተደረገባቸውም እንጂ.......እንደዚህ በጥበብ ዙርያ የተሰሩ ሌሎች ጥናቶች ካሉ ብትጠቁሙኝ!!!!
ReplyDelete