“በኤርትራ
የወታደሩን ትግል ፈር ያስያዙትና የሚያንቀሳቅሱት እነ ነሲቡ ታዬ ነበሩ። ፍስሐ ደስታ አጋፋሪ ነዉ። ከአብዮቱ በፊት ፖለቲካ ዉስጥ
ብዙ የማይገባ ሰዉ ቢሆንም ከማንም ያላነሰ አስተዋፆ አድርጓል። ነገሩ ሁሉ እየጋለ መጥቶ ዉጥረት በበዛብኝ ወቅት አንዳንድ ቀልዶችን
በመናገር ፊቴን የሚያፈካዉ ሰዉ ነበረ። ለአስተባባሪ ኮሚቴ “ደርግ”
የሚለዉን ስያሜ የሰጠዉ ናደዉ ዘካሪያስ ነዉ።“ [1] ሌተናል ኰሌኔል መንግስቱ
ሀይለማሪያም
-----------------------
[1]: ምንጭ፡
ገነት አየለ አንበሴ -የሌተናል ኰሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም ትዝታዎች ቁ.1 መጽሐፍ
“<<ደርግ>> የሚለዉ ቃል <<ደረገ>> ከሚለዉ የግዕዝ ግስ የመጣ/ የተወረሰ ነዉ።
አድስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ሲተረጉመዉ “ደረገ” ተስማማ ገጠመ አንድ ሆነ
<<አበረ>> በማለት የደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት ገልፆታል። ይሁን እንጅ ቃሉ የቆየ ቢሆንም
በገጠር በኩል እስከ ተወሰነ አመታት ድረስ በተለይ አረሶ አደሩ “ደርግ” የሚለዉን ቃል ትርጉሙ ገብቶት ነበር ለማለት ይቸግራል።
ለምሳሌ አንዳንዶች ደርግ ለማለት የሚበረግግ፣ ቀንድ ያለዉ፣ የሚዋጋ፣ መያዣ መጨበጫ የሌለዉ፣ የሚያስፈራ የሚያስበረግግ ወዘተ በማለት
ይተረጉሙት ነበር። እንዲያዉም አንዳንዶች ደርግን የሰዎች ማስፈራሪያ እያደረጉ አንድን ህፃን/ልጅ ለማስደንገጥ ሲሉ አዋ! ደርግ
መጣ የሚሉ ተደምጠዋል።” [2] ታክሎ ተሾመ
----------------------
[2]: ምንጭ፡
ታክሎ
ተሾመ - የደም ዘመን
No comments:
Post a Comment