ልጄ ሆይ በዚህ አለም ሀይለኞች ገንዘብና እዉቀት ሁለቱ ብቻ ናቸዉ። ገንዘብ እና
እዉቀት ያለዉ ሰዉ እስከ ጊዜዉ ደስ ብሎት ይኖራል። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ገንዘባቸዉን በማይረባ ጉዳይና ሰዉን በማጥፋትና ራሳቸዉን ብቻ ለመጥቀም አድርገዉ ሀይላቸዉ ይደክማል። ገንዘባቸዉን
ለንግድና ለድሃ እዉቀታቸዉንም ለስራና ለሰዉ ጥቅም የሚያደርጉ ሰዎች ግን በሀይል ላይ ሀይል እየጨመሩ ይኖራሉ። እነሆ ለዚህ አንድ
ምሳሌ እነግርሀለሁ። ነጭ ስንዴ በባለሙያ እጅ ሲሆን ያማረና የጣፈጠ እንጀራ ይሆናል። በባለሙያ እጅ ያልሆነ እንደሆነ ግን እንደ
ዘንጋዳ እንጀራ ይሆናል። ገንዘብና እዉቀትም በደግ ሰዉ እጅ ሲገቡ ለመልካም ነገር ይሆናሉ። በክፉ ሰዉ እጅ ሲጉ ግን ለጥፋት ነገር
ብቻ ይሆናሉ።
ልጄ ሆይ የምትሰራዉን ስራ ሁሉ ሰዉ ቢያየዉ ቢሰማዉም አይጎዳኝም ብለህ ትሰራዉ እንደሆነ
ነዉ እንጅ አይታይብኝም አይሰማኝብም ብለህ አትስራዉ። አንተ ምንም
ተሰዉረህ ብትሰራዉ ከተሰራ በሗላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም። /ብላቴን ህሩይ ወልደ ስላሴ- ወዳጄ ልቤና ሌሎችም/
No comments:
Post a Comment