ሀገራችን
ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የረጅም ዘመን የታሪክና የባህል መሰረቶች ያሏት ሀገር ብትሆንም ዛሬ ዛሬ የምራባዊያንን አኗኗርና አስተሳሰብ አንጋጠን በመመልከትና ያሉንን ባህላዊና
ሀገራዊ እሴቶችን አንድም ባለ ማስተዋል አንድም ሗላቀር አድርጎ በመሆሰድ ምስኪን ልጆቿ “አባቱን አያዉቅ አያቱን ይናፍቃል” እንዲሉ በማያገባንና በመማይመለከተን የምዕራባዊና አስተሳሰብ ተጠልፈን ለመዉደቅ
እየታተርን እንገኛልን። አገር ማለት ይለናል ታሪክና ምሳሌ 3ኛ መጸሐፍ
… “አገር ማለት በታሪክ በቋንቋ በሀይማኖት፣ በልምድ፣ በተስፋ፣ በደስታና
በመክራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው። እግዚአብሔር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት
በማድረጉ፤ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍቅርዋ በአጥንትና በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ፣ እናት ማለት ነው። አገር አባት፣ እናት፣ ዘመድ፣
ምግብ ፣ጌጥና ሀብት በመሆኑ፤ ድህንትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ
የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው”።
እዉነታዉ
ይኸ ሆኖ ሳለ ግን በተለይም ዛሬ ላይ ያለዉ አድሱ ትዉልድ ስለ ተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮችና የታሪክ እዉነቶች ከመጠየቅና ከመዎያየት
ይልቅ ሌሎች የምዕራባዊያን እንቶፈንቶ ወሬዎች ለመስማትና ለማዎቅ የማይፈነቅለዉ ድንጋይ ያለመኖሩን በንቃት ለታዘበ ቅን ዜጋ ያለንበት
ሁኔታ እጅግ አስፈሪ መሆኑን ለመገንዘብ አያዳግትም። ለዚህም ነዉ ስለ አድዋ ጦርት ወይም ስለ አጼ ቴዎድሮስ የማይበገር ክንድና
ለእናት ሀገራቸዉ ስለከፈሉት ዋጋ ከመመስከርና ከመዘከር ይልቅ ስለ ሪሃና አለባበስና አዋዋል መደስኮር የሚቀናዉ ትዉልድ እየተፈጠረ
ያለዉ። እዉነታዉ ግን ይኸ ሳይሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ዜጎች
ሊኮሩባቸዉና አልፎ ተርፎም ሌሎች የዉጭ ሰዎችን ቀልብ ጭምር የሚያማልሉ በርካታ ሀገራዊ እሴቶችና ትዉፊቶች ያሏትና ምን አልባትም
ዛሬ ምራባዊያን እንዳድስ የሚያቀብሉንን በርካታ ጉዳዮች ቀድማ ያዎቀችና ለአለም ያስተዋዎቀች ሀገር እንደሆነች ታሪክ የማይክደዉ
ሀቅ ነዉ። የዚህ
አምድ ዋና አላማ እነዚህንና ሌሎች በርካታ የታሪክ ሁነቶችን ነቅሶ በማዉጣትና ለዉይይት በማቅረብ ለአንባቢያን ስለ ሀገራቸዉ የተሻለ
ግንዛቤ በማስጨበጥ ብሔራዉ ስሜትን ማጫር ነዉ።
No comments:
Post a Comment