Saturday, May 12, 2012

የኢቲቪ ነገር!

“ኢቲቪ” አድማጭ ተመልካቾቹን ለ“ቲቢ” በሽታ እንደሚያጋልጥ መሐመድ ሰልማን በቅርቡ ባሳተመ መፀሐፉ ደርሸበታለሁ ብሎናል።   እንዴት? ደግሞ፣  “ሴት አያቴ ኢቲቪን ስትመለከትና የማይመስል ነገር ስትሰማ ያስላታል፤ እናም ኢቲቪ ሳምባዋን ሳይነካት አይቀርም”  በማለት ምልክቱንና ምክንያቱን ያብራራልዎታል። ለወንድ አያቴም ቢሆን የጨጓራ ህምም መነሾ ሆኗል ሲልም መሐመድ ኢቲቪን ይወቅሳል።  “ኢቲቪ” ግን በመሐመድ ሴት አያና ወንድ አያ ብቻ አላቆመም፣  አሁን አሁን ሁላችንንም እያሳለን ነዉ። እኔማ ብሶብኛል!  ቅርቡ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳረጋገጠዉ ከሆነ ደግሞ የሀገር ዉስጥ ዜናዎችና ልማታዊ የቅኝት ፕሮግራሞች የበሽታዉ አይነተኛ ተሸካሚ ቫይረሶች በመሆናቸዉ ቴሌቪዠ በመዝጋትና እነዚህ ፕሮግራሞ ከማየትም ሆነ ከመስማት በመቆጠብ የበበሽታዉን ዘጠና በመቶ ስርጭት ት እንደሚቻል አረጋግጫለሁ ብሏል


አንድ ወዳጀ ግን በዚህ ሀሳብ አይስማም! 
“ኢቲቪ የራሱ የሆነ የዜና አዘጋገብና አቀራረብ ስልት አለዉ፡ ብዙዎቻችን ግን ይህን ስልት ባለማወቃችን ኢቲቪን ፍትሀዊ አይደለም በማለት እንኮንናለን ይህ ግን ስህተት ነዉ” በማለት ያብራራል። እንዴት? ካላችሁት ደግሞ  “ኢቲቪ” የሚዘግበዉ ትክክለኛዉን ነባራዊ ሁኔታ ቢሆንም፤ ብዙን ጊዜ ግን ዜናዉ አየር ላይ ሲዎጣ የትክክለኛዉ ዜና ተቃራኖ (opposite) ነዉ የሚቀርበዉ። አልፎ አልፎ ደግሞ አንዳንድ ወዳጆችንና ባለዉለታዎችን ላለማስቀየም ዜናዉን በቀጥታ ከመረብ ይልቅ በቅኔ መልክ ሊቀርብ ይችላል። በመሆኑም የሌሎች ታዋቂ ሚዲያዎችን የዜና አቀራረብ ሰልትን ከመኮረጅና ከመከተል ይልቅ የራሱን ሐገራዊ ስልት በመፍጠሩ <ኢቲቪ> ሊሞገስ እንጂ ሊወቀስ አይገባም” በማለት ያስረዳችሗል። በመሆኑም ይላል ይህዉ ጉደኛ ወዳጄ፤ “በመሆኑም ችግሩ ያለዉ ከ <ኢቲቪ> ሳይሆን ከአድማጭ ተመልካቹ ነዉ በማለት እቅጩን ይነሗል። እሺ! በማለት ደግሞ እንዲቀጥል ከጋበዛችሁት፣ እናም በማለት ዲስኩሩን እንዲህ ሲል ይቀጥላል፣ 

“እናም አንድ የኢቲቪን ዜና የሚከታተል ሰዉ ትክክለኛዉን ዜና ለማግኘት/ለመረዳት/ ከፈለገ፣ በመጀመሪያ አየር ላይ የዋለዉን ዜና መዉሰድ/መስማት/ ከዚያም የዜናዉን ተቃራኖ (opposite) በመዉሰድ ትክክለኛዉን ዜና ማግኘት ይገባዋል” ሲል ደረስኩበት ያለዉን አድስ የኢቲቪን ዜና ለመረዳት የሚያግዝ ፎርሙላ በጥቂቱ ያካፍላችሗል።  ምሳሌ ካላችሁት ደግሞ፤ ለምሳሌ ይላችሗል፣ ለምሳሌ አየር ላይ የዋለዉ ዜና  “አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት የ11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን መንግስት አስታዎቀ” ከሆነ ትክክለኛዉ ዜና ደግሞ  “አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አመታት የ 11 በመቶ የኢኮኖሚ ዉድቀት ማስመዝገቧን መንግስት አስታዎቀ”። ይሆናል ማለት ነዉ።  አገርህ በለፀገች! ቢሉት “እኔ የት ሄጄ?“ አለ ለምኖ አዳሪ! እንዲለን በሀይሉ ገ/እግዚያብሔር::


እኔ ግን ፎርሙላዉ ለሀገር ዉስጥ ዜናዎችና ለአንዳንድ የዉጭ ሀገር ዘገባዎች ካልሆነ በስተቀር በቀጥታ ስርጭት ለሚተላለፍ የእግርኳስ ግጥሚያዎችና የሙዚቃ ክሊፓች እንደማይሰራ ላስረዳዉ ሞክራለሁ። እስኪ እርሰዎ ደግሞ ከኢቲቪ ዜና እዎጃ ላይ ተቀንጭቦ ከተወሰደዉና ከዚህ ቀጥሎ ከቀረበዉ ዜና ላይ፣ ከላይ የቀረበዉን ፎርሙላ መሰረት በማድረግ የዜናዉን ትክክለኛ ትርጉም ያግኙ!

“በአድስ አበባ የሚገኙ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የህዳሴዉ ግድብ ሙሉ ለሙሉ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ምንም አይነት የደመወዝ ክፍያ እንደማይፈልጉ አስታወቁ። መንግስት በበኩሉ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቅርቡ ያስመዘገበችዉን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት አስታዉሶ ሰራተኞቹ ሙሉ ደመወዛቸዉን ለልማት ለማዋል ያሳዩትን ቀና ትብብር በማድነቅ ከደመወዛቸዉ በተጨማሪ በባንክ ያስቀመጡት ገንዘብ ካለ በማዉጣት ለዚህ የተቀደሰ አላማ እንዲያዉሉት ጥሪዉን  አስተላልፏል።”

------------------------------------------------------------------------------- -------------------------------------------------------------------------------

No comments:

Post a Comment