በአንድ መለስተኛ የገበሬ ጎጆ ቤት ዉስጥ የሚኖሩ ሶሰት የተለያዩ የቤት እንስሳቶች (አንድ ዶሮ፣
አንድ አሳማና አንድ ላም) ስብሰባ ላይ ተቀምጠዋል ። ዋናዉ የተሰበሰቡበት ምክንያት ደግሞ ቁጥራቸዉ ትንሽ በመሆኑና ሁሉም አንድ
አንድ ብቻ በመሆናቸዉ የሆነ ችግር ወይም አደጋ ቢገጥማቸዉ በተናጥል ለመከላከል ከባድ መሆኑን በማመናቸዉና ይህንኑ አሳሳቢ ችግር
እንዴት በጋራ ህብረት ፈጥረዉ መከላከል እንዳለባቸዉ ዉይይት ለማካሄድና የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ነዉ። ሶስቱም ለብዙ ሰአታት ከተከራከሩና ከተጨቃጨቁ በሗላ፣ “ሁሉም ቤት ዉስጥ የሚደረግን ማንኛዉም እንቅስቃሴ በንቃት መከታተል እንዳለባቸዉና
ለሶስታቸዉም አልያም ከሶስታቸዉ ላንዳቸዉ ሊያሰጋ የሚችልን ማንኛዉንም እንቅስቃሴ ሲደረግ ያየ አልያም የሰማ አካል ለሌሎች የቡድኑ
አባላት በፍጥነት ማሳወቅ እንዳለበትና ችግሩ በተከሰተ በአጭር ጊዜ ዉስጥም ሶስቱም አስፈላጊዉን ትብብር በጋራ በማድረግ ችግሩን
መፍታት እንዳለባቸዉ የሚደነግግ የጋራ ስምምነት ላይ ይደረሳሉ።
Tuesday, May 22, 2012
Friday, May 18, 2012
Monday, May 14, 2012
እሺ! ይኸንስ የሞት ብድር ማን ይክፈለዉ?
1970፣ እሁድ፣ ከጧቱ 4፡10
ከአጭር
ጊዜ የስራ ቆይታ በሗላ ክፍለ ሀገር ወደሚኖሩት ቤተሰቦቹ በቅርቡ የተመለሰዉ ታዘበ ወልዴ፣ እንደ አረንጓዴ ስጋጃ ተዘርግቶ በተንጣለለ ትልቅ ግቢ መስክ ላይ ብርኩማ ላይ ተቀምጦ የጧት ፀሀይ እየሞቀ ነዉ። ታዘበ
ከብዙ ጊዜ ድካምና ልፋት በሗላ ከአድስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ ተመርቆ እዛዉ አድድስ አባባ ዉሰጥ የሚገኝ አንድ የመንግስት
ከፈተኛ መስሪያ ቤት ዉስጥ ተቀጥሮ መስራት ከጀመረ ገና ስድስት ወሩ ነዉ። የቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ በመሆኑና ቤተሰቦቹ ተምሮ እዚህ
ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከነበራቸዉ ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ብዙ መስዋዕትነትን በመክፈል ነበር አስተምረዉ ለዚህ ደረጃ ያበቁት። በተለይ
እናቱ የወርቅዉሀ ታደሰ የእሱ ተከታይ የሆነችዉን ሴት ልጃቸዉን አመለወርቅ ወልዴን በጀርባቸዉ አዝለዉ፣ በአንድ እጃቸዉ የዉሀ መቅጃ
በሌላ እጃቸዉ ደግሞ የከብቶች መመለሻ ዱላ ጨብጠዉ፣ ከሁሉም በላይ ላይ ደግሞ ፋታ የማይሰጠዉን የቤት ዉስጥ ስራ አንድም ቀን ደከመኝና
ሰለቸኝ ሳይሉ ያለ ማንም አጋዥ ብቻቸዉን እየማሰኑ ነበር አስተምረዉ እዚህ ያደረሱት። አባቱ ወልዴ ታፈረም ቢሆኑ፣ በደከመ ጉልበታቸዉ
ብቻቸዉን ሞፈርና ቀንበር እየተሸከሙ፣ ከደረቀ መሬት ጋር እየታገሉና ከአመት አመት እያመረቱ፣ ለልጃቸዉ የሚሆን በቂ የትምህርት
ጊዜን አንድም ቀን ሳያጓድሉ ነዉ አስተምረዉ ዛሬ ላለበት ደረጃ ያበቁት።
የዚህን ፋይል የፒዲኤፍ (PDF) ቅጅ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!
የዚህን ፋይል የፒዲኤፍ (PDF) ቅጅ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!
Saturday, May 12, 2012
የኢቲቪ ነገር!
“ኢቲቪ” አድማጭ ተመልካቾቹን ለ“ቲቢ” በሽታ እንደሚያጋልጥ መሐመድ ሰልማን በቅርቡ ባሳተመዉ መፀሐፉ
ደርሸበታለሁ ብሎናል። እንዴት? ካሉ ደግሞ፣ “ሴት አያቴ ኢቲቪን ስትመለከትና የማይመስል ነገር ስትሰማ ያስላታል፤ እናም
ኢቲቪ ሳምባዋን ሳይነካት አይቀርም” በማለት ምልክቱንና ምክንያቱን
ያብራራልዎታል። ለወንድ አያቴም ቢሆን የጨጓራ ህምም መነሾ ሆኗል ሲልም መሐመድ ኢቲቪን ይወቅሳል። “ኢቲቪ” ግን በመሐመድ ሴት አያትና ወንድ አያት ብቻ አላቆመም፣ አሁን አሁን
ሁላችንንም እያሳለን ነዉ። እኔማ ብሶብኛል! በቅርቡ
የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳረጋገጠዉ ከሆነ ደግሞ የሀገር ዉስጥ ዜናዎችና ልማታዊ የቅኝት ፕሮግራሞች የበሽታዉ አይነተኛ ተሸካሚ ቫይረሶች በመሆናቸዉ
ቴሌቪዠን በመዝጋትና
እነዚህን ፕሮግራሞች ከማየትም
ሆነ ከመስማት በመቆጠብ የበበሽታዉን ዘጠና በመቶ ስርጭት መግታት እንደሚቻል አረጋግጫለሁ ብሏል።
Thursday, May 10, 2012
ማራኪ ገጾች
“በኤርትራ
የወታደሩን ትግል ፈር ያስያዙትና የሚያንቀሳቅሱት እነ ነሲቡ ታዬ ነበሩ። ፍስሐ ደስታ አጋፋሪ ነዉ። ከአብዮቱ በፊት ፖለቲካ ዉስጥ
ብዙ የማይገባ ሰዉ ቢሆንም ከማንም ያላነሰ አስተዋፆ አድርጓል። ነገሩ ሁሉ እየጋለ መጥቶ ዉጥረት በበዛብኝ ወቅት አንዳንድ ቀልዶችን
በመናገር ፊቴን የሚያፈካዉ ሰዉ ነበረ። ለአስተባባሪ ኮሚቴ “ደርግ”
የሚለዉን ስያሜ የሰጠዉ ናደዉ ዘካሪያስ ነዉ።“ [1] ሌተናል ኰሌኔል መንግስቱ
ሀይለማሪያም
-----------------------
[1]: ምንጭ፡
ገነት አየለ አንበሴ -የሌተናል ኰሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም ትዝታዎች ቁ.1 መጽሐፍ
“<<ደርግ>> የሚለዉ ቃል <<ደረገ>> ከሚለዉ የግዕዝ ግስ የመጣ/ የተወረሰ ነዉ።
አድስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ሲተረጉመዉ “ደረገ” ተስማማ ገጠመ አንድ ሆነ
<<አበረ>> በማለት የደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት ገልፆታል። ይሁን እንጅ ቃሉ የቆየ ቢሆንም
በገጠር በኩል እስከ ተወሰነ አመታት ድረስ በተለይ አረሶ አደሩ “ደርግ” የሚለዉን ቃል ትርጉሙ ገብቶት ነበር ለማለት ይቸግራል።
ለምሳሌ አንዳንዶች ደርግ ለማለት የሚበረግግ፣ ቀንድ ያለዉ፣ የሚዋጋ፣ መያዣ መጨበጫ የሌለዉ፣ የሚያስፈራ የሚያስበረግግ ወዘተ በማለት
ይተረጉሙት ነበር። እንዲያዉም አንዳንዶች ደርግን የሰዎች ማስፈራሪያ እያደረጉ አንድን ህፃን/ልጅ ለማስደንገጥ ሲሉ አዋ! ደርግ
መጣ የሚሉ ተደምጠዋል።” [2] ታክሎ ተሾመ
----------------------
[2]: ምንጭ፡
ታክሎ
ተሾመ - የደም ዘመን
Subscribe to:
Posts (Atom)




