Thursday, July 19, 2012
Thursday, July 5, 2012
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ/ን…
መቸም ኢትዮጵያ ዉስጥ አድስ የተጀመረን ነገር ወይም የነበረን አገልግሎት ሲቻል በአለም፣ ካልሆነ በአፍሪካ እነዚህ ሁለቱ ካልተሳኩ ደግሞ “በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ” በሚል ተቀጥላ ማስተዋወቅ በህግ ተደንግጎ የተቀጠ ግደታ እስከሚመስል ድረስ ከግለሰብ እስከ መንግስት ተቋማት ድረስ የተለመደ ነዉ። ምናልባትም የዚህ አይነት የማስታዎቂያ ተቀጥላዎችን በብዛት በመጠቀም በአለም የመጀመሪያዎቹ ሳንሆን አንቀርም (lol አላችሁ!)። በእዉቀቱ ስዩም “የቤተሰቦቼ ሁለተኛ ልጅ በመሆን የመጀመሪያ ነኝ” ሲል በአሽሙር ልክልካቸዉን እንደነገራቸዉ ማለቴ ነዉ፡፡ በርግጥ ከኢትዮጵያም አልፈዉ በአለም ደረጃ ለመተግበር ቀርቶ ለማሰብ እንኳን የሚከብዱ በርካታ ስራዎችን ቀዳሚ በመሆን ያበረከቱ አሊያም ያስተዋወቁ የትየለሌ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ እሙን ነዉ። እነዚህን ኢትዮጵያዊያንም “የመጀመሪያዉ” በሚል የማሞካሻ የማዕረግ ተቀጽላ መጠራት ቢያንሳቸዉ እንጂ የሚበዛባቸዉ አይሆንም። ምናልባትም ዛሬ ላይ ያሉ ማስታዎቂያ ነጋሪዎችም በእዉቀቱ እንዳለዉ “የመጀመሪያዉ” የሚለዉን ተቀጽላ “እግዚያብሔርም በመጀመሪያ ሰማይና ምድርን ፈጠረ” ከሚለዉ የመጸሐፍ ቅዱስ ቃል ሳይሆን ከነዚህ ኢትዮጵያዉያን የክብር ስም ላይ ይሆናል ላፍ አድርገዉ የወሰዱት።
Subscribe to:
Posts (Atom)