Thursday, August 30, 2012

ይህ እኮ የእኔ እንጂ የአንተ አገር አይደለም!

 
ፀሐፊ [ሞረሽ] ምድብ [ኑሮና ፖለቲካ]


በዚህ ልንጨርሰው ባገባደድነው አመት ጥቅምት ወር ውስጥ ለስራ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ተነስቼ ወደ ሀገሪቱ ምዕራብ ክፍል መዳረሻየን ጋምቤላ ክልል ወደ ምትገኝ ዲማ ከምትባል ትንሽ የገጠር ከተማ አድርጌ ተጉዤ ነበር። በመጀመሪያው ጉዞየ ከአዲስ አበባ ተነስቼ ጂማ አደርኩ። በሚቀጥለው ቀን ደግሞ በሌላ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተሳፍሬ ጉዞየን ወደ ሚዛን ከተማ ቀጠልኩ። ከጂማ እስከ ሚዛን ያለው ጉዞ ስምንት ያህል ሰዓት ፈጀብን። ከጂማ - ሚዛን ያለው መንገድ የአስፓልት ንጣፍ ቢጀመርለትም አብዛሃኛው የመንገዱ ክፍል በፒስታ የተሸፈነ በመሆኑና ኮረኮንቻማ ስለሆነ ጉዞው በጣም አድካሚ ነበር።


 መዳረሻዬ ወዳደረኳት ዲማ ከተማ ደርሼ ቶሎ ለመመለስ ስለፈለኩ ሚዛን አውቶብስ ተራ ከወረድኩ በሗላ ቀጥታ ወደ ዲማ የሚወስደኝን መኪና ነበር ማፈላለግ የጀመረኩት ። የዕለቱን የምሳ መርሃ-ግብርም የፈፀምኩት መኪናውን ካገኘሁት በሗላ ነው ። ይህ ከላይ ሳወጋችሁ የቆየሁት ዋናው የጉዞ ትውስታዬ አይደለም። እንድሁ አነሳሴንና ዋና ዋና ያልኳቸውን  የጉዞ ትውስታዎች እስኪያጋጥሙኝ ድረስ ያለፍኩበትን በደምሳሳው ለማሳዬት እንጂ ።

Friday, August 24, 2012

የመጨረሻዋን ሰዓት በቤተ መንግስት


ጥንቅር [ሞረሽ] ምድብ[ማራኪ ገፆች]

የአዳራሹ መጋረጃዎች ስላልተከፈቱ ጭልምልም ብላል። ሀይለስላሴ ዙፋናቸው ላይ ፀጥ ብለው ተቀምጠዋል። ጊዜያቸውን ሲያጣብብ የነበረው የሰው ጋጋታ ደንብና መመሪያ ማውጣት በመቆሙ አካባቢው ጭር ብሏል ። በመጨረሻ የማያውቁት ሰው ውሳኔዎችን እየሰጠ እንደሆነ ደመደሙ ።

ራስ ካሳም በበኩላቸው ፕሮቶኮሉን ጥሰው ሌሎቹ የምክር ቤት አባላት እየተከተሏቸው አዳራሹን በርግደው ገቡ ። ንጉሰ ነገስቱ በራሶቹ መምጣት አልተገረሙም ። ምንም እንኳን መረጃ የሚያቀብላቸው ሰው ባይኖርም፣ ንጉሱ ቁጣ እንደሚቀሰቅስና ያንንም ተከትሎ የምክርቤቱ አባላት ፍርሃታቸው እንደሚጨምር ያውቃሉ።