Wednesday, June 27, 2012
Wednesday, June 20, 2012
ግን ለምን እንፈራለን? (ክፍል አንድ)
የአለፈዉ ሳምንት አድስ ጉዳይ መጽሔት አብይ አርዕስት አድርጎ ይዞት የወጣዉ ሀሳብ በአሁኑ ወቅት ያሉትን የኢትዮጵያ ምሁራንን በፍርሃት ተሸብቦ የመቀመጥን ነገር ነበር። አድስ ጉዳይ “የፍርሃት ሀገር ዜጎች፣ ‘ኦሜርታ’!” በሚል አርዕስት ይህንኑ ጉዳይ የዳሰሰበትን ማራኪ ጽሁፍ ያስነበበን ሲሆን እነዚህኑ ከልክ ባለፈ ፍርሃት ተሸብበዉ የሚገኙ የዘመናችንን ምሁራንን፣ “ዉሃ ዉስጥ ተኝተዉ የሚያልባቸዉ ምሁራን” ሲል ነበር የገለጻላቸዉ። በርግጥም አዋቂና ችግር ፈች የሚባለዉ የአንድ ሀገር የተማረ ዜጋ የራሱንና የሌሎችን መብት ለማስከበር ከመትጋት ይልቅ በፍርሃት ተሸብቦና ተሳስስሮ ከተቀመጠ ቢያንስ መብትና ግደታዉን እንኳን በቅጡ ለይቶ የማያዉቀዉ ሌላኛዉ ያልተማረ ህብረተሰብ ክፍል ደግሞ ከፍርሃትም በላይ በሆነ ጭንቅ ዉስጥ እየኖረ እንደሆ መገመት አያዳግትም።
Friday, June 1, 2012
የመዝሙረ ዳዊት ሚስጥሮች
መጸሐፍ ቅዱስ በአለማችን በብዛት ከተነበቡና
ወደ በርካታ የተለያዩ የአለም ቋንቋዎች ከተተረጎሙ መጸሐፍት መካካከል አንዱና ምናልባትም በአንደኝነት ሊጠቀስ የሚችል መጸሐፍ መሆኑ
አያጠራጥርም። ምንም እንኳን መጸሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈዉ? የሚለዉ ጥያቄ በተለያዩ ሰዎች የተለያየ መልስ የሚሰጥበት አከራካሪ ጉዳይ
ቢሆንም እንደዛሬዉ መጸሐፍት እንደልብ ባልነበሩበት ዘመን ለብዙዎች
የጥበብ ምንጭና የእምነት መንገድ ጠራጊ የሆነ፣ ዛሬም ድረስ ክርስትናን የእምነት ፍልስፍናቸዉ መሰረት ላደረጉ በርካታ የእምነቱ
ተከታዮች የእምነት-ማዕዘን በመሆነ እያገለገለ ያለ ታላቅ መጸሐፍ ነዉ፣ መጸሐፍ ቅዱስ። መጸሐፍ ቅዱስ በዋናነት ብሉይ-ኪዳንና አድስ-ኪዳን በሚባሉ ሁለት መሰረታዊ ክፍሎች (ቅጾች) የተዋቀረ
መጸሐፍ ሲሆን እነዚህም ሁለት ቅጾች እያንዳንዳቸዉ በርካታ ምራፎችንና የመጸሐፍ ክፍሎችን በዉስጣቸዉ አካተዉ የያዙ ናቸዉ። ከነዚህ በርካታ የመጸሐፍ ክፍሎች መካከል “መዝሙረ ዳዊት” በመጀመሪያዉ የመጸሐፍ ቅዱስ ቅጽ (በብሉይ ኪዳን) ስር ተካቶ የሚገኝ የመጸሐፍ
ቅዱስ ክፍል ሲሆን ምንም እንኳን “መዝሙረ ዳዊት” መቸና በማን ተጻፈ የሚለዉ ጉዳይ አከራካሪና እራሱን የቻለ ጥናትን የሚፈልግ ጉዳይ ቢሆንም
Subscribe to:
Posts (Atom)